Posted On August 18, 2026

ተስፋን የተከሉ እጆች ከበረከታቸው ተጠቃሚ ሁነዋል

admin 0 comments
>> Uncategorized >> ተስፋን የተከሉ እጆች ከበረከታቸው ተጠቃሚ ሁነዋል

ሐምሌ 9/2018 ዓ.ም አሶሳ፤

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ሐጂ ባበክር ኸሊፋ በሆሞሻ ወረዳ የፍቃዱ ነመራ የተቀናጀ እርሻ ጎበኙ፤

በፍቃዱ ነመራ የተቀናጀ እርሻ ልማት ድርጅት በአንድ አመት ተኩል ጊዜ የተተከሉ የብርቱኳን፣ የሎሚ፣ የሙዝና የሮማን ፍራፍሬ ችግኞች ለገበያ እየቀረበ መሆኑን አቶ ፍቃዱ ነመራ የድርጅቱ ባለቤት ተናግረዋል፤

የክልሉ መንግስት በሰጠው የግብርና ኢንቨስትመንት በአትክልትና ፍራፍሬ እና በእንስሳት ልማት በአጭር ጊዜ ውጤታማ መሆኑን አቶ ፍቃዱ ነመራ ተናግረዋል፤

በተጨማሪ እሸት በቆሎ፣ አንጮቴ፣ ቆጮ፣ ድንችና ካዛባ ከበጋ እስከ ክረምት ለገበያ እያቀረቡ መሆኑን ተናግረዋል፤

የግብርና ቢሮ ኃላፊ ክቡር ሐጂ ባበክር ኸሊፋ ችግኝ በመትከል በረከትን መቀበልና ለትውልድ ማስቀመጥ እንደሆነ ተናግረዋል::

Related Post

ኢትዮጵያ ታምርት

የራስን አቅም በአግባቡ መጠቀም ማለት እንደዚህ ነው ። አቶ ፍቃዱ ነመራ የግብርናውን ዘርፍ አጠናክረው በማስቀጠላቸው…

የኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ጉዞ በጠንካራ መሠረት ላይ እየተገነባ ይገኛል! ም/ል ጠቅላይ ሚኒስተር ተመስገን ጥሩነህ

"በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሆሞሻ ወረዳ የተመለከትነው የተቀናጀ የእርሻ ልማት ደግሞ የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ለምናስበው ሽግግር…

በተፈጥሮ መካከል የሚገኝ ምቹ የመኖሪያ ስፍራ

እርሻችን ትኩስና ተፈጥሯዊ ምርቶችን ብቻ ሳይሆን፣ በተፈጥሮ ውበት መካከል ለመዝናናትና ለመቆየት ምቹ የመኖሪያ አገልግሎትም ያቀርባል።…